skip to Main Content

ስደተኞችን ለምትደግፍና ከስደተኞች ጋር ለምትተባበር ኤሮፓ እንስራ!”
pour une Europe migrante et solidaire

እኛ፡ የዚህ ማኒፈስቶ ፈራሚዎች፡ ወደ 2019 የኤሮፓ ምርጫ ልናቀርበው የምንፈልገው ሊስት መነሻው የተረዳነው ነገር በመኖሩ ነው፥ ዛሬ በስደተኞት ላይ ሲፈጸም የምናየው የፖለቲካ ግፍ፡ በኣጠቃላይ በድሀ ወገኖች ላይ ያላትን ዘለቅ ያለ አስተያየት ይመሰክራል።

የስደተኞች ፖሊሲ ብኤሮፓ ፕሮጀክት ውስጥ ትልቅ ቦታ ስለሚይዝ የሃያ ኣንደኛው ክፍለ-ዘመን ኤሮፓን በምትከተለው በጎ ኣቀባበልና ባላት የመደጋገፍ ፕሪንሲፕል ማስገምገም ኣለበት ብለን ስለምናምን ይህንን ሊስት ኣጥብቀን እንሰራበት ኣለን። ደሞክራቲክ መንግስቶች ይህንን ፕሪንሲፕል ባለማክበር የኤሮፓ ባህል መልእክትን ረስተውታል።

ኤሮፓ ስደተኞችን ከድምበርዋ ባሻግር ስታባርር የራሷን ቫልዩ (values) እና ይሰው ልጅን መሰረታዊ መብት ትረግጣለች። ይህ ድርጊት የተከፋቸውን ህዝቦችን፡ ኣዲስ ስርዓት ሊበራሊዝም የገፋቸውን ጭቁኖችንና ስራና መኖርያ የሌላችውን ሰዎች ከማሕበረ-ሰቡ እንደምታገልለው ተግባር ጋር ተመሳሳይ ነው።

ኤሮፓ ከጥንቱም ጀምሮ፡ ከሁሉም በኩል በሚተላለፉ የስደተኞች መስመሮች ላይ የታነጸች ናት። እንዲያውም፡ የብዙ ዓይነትነቷና የሃብቷ ምንጮች እነዚሁ ኣዳዲስ ህዝቦች ናቸው። ስደተኞችን የሚጨቁን ፖሊሲ የሚከተል ብሄራዊ ኣገር በመሃሉ ላይ ባሉት ድሃዎች ሳይቀር ይጨክናል። 

“ስደተኞችን ለምትደግፍና ከስደተኞች ጋር ለምትተባበር ኤሮፓ እንስራ!” (Pour une Europe migrante et solidaire)የሚሰየመው ሊስት ከሁሉም ወገኖች ሲቪል ሶሳይቲ፡ ከሁሉም ማሕበራዊ ደረጃና ክሁሉም ዕድመ የመጡ፡ ኤሮፓ በስደተኛ ፖሊሲዋ ኢንስቲትዩሽኖችዋን መርሳትዋ የሚቃወሙ ሰዎችን ያሰባስባል።

ኤሮፓ ስደተኞችን ለመቀበልና ለመከናከን ያላትን ዓቅም ሆነ ብላ መቀነሷና መርሳቷ፡ የሚረዷቸውን ሰዎች የማገዝ መብትን በመናቅ መቅጣቷ፡ በሓያል ግጭቶችና ሙስና ውስጥ በተጨማለቁ መንግስታት ወይ በክሊማ ለውጥ ምክንያት ከኣገራቸው ለሸሹ ስደተኞች የባሕር ወደቦቿን መዝጋቷ እንቃወማለን። 

ሴቶችና ልጆች የሚገኙባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኣካባቢ ጥረትና በበጎ ኣድራጎት ማሕበራትና ብመተጋገዝ ስምምነቶች የሚረዱበት ዕድል እያለ፡ በመዲተራኒያን ባሕርና በሳሃራ ምድረ-በዳ መሞት መቀጠላቸውን ወይ በኮንቲነንታችን በመጥፎ ኑሮ መሰቃየታቸውን እንቃወማለን። ሲቪል ሶሳይቲ ስደተኞቹን በመቀበል ረገድ ድርሻውን መወጣት ኣለበት። ቢሆንም፡ ስራውን ለማደልደል፡ ድምበር መቆጣጠርንና ሁነታ ሰደተኞችንና ተቀባይ ሕብረተ-ሰብ ውስጥ የሚውሃሃዱበት ኣገብባን የሚመለከቱ ኣዳዲስ ፖሊሲዎች በኤሮፓ ደረጃ ያስፈልጋሉ።

ድሃ ኣገሮች መካከል ወይ ወደ ኤሮፓ የሚደረገው ስደት ግዜያዊ ወይ የላይ ላይ ክስተት ሳይሆን፡ በተለይ በአንቫይሮንመንት ችግር ተባብሶ በከፍተኛ ደረጃ የሚቀጥል ይሆናል። ለመጪውም ግዜ፡ ብኤሮፓ ይሁን ብዓለም ደረጃ፡ በኣንድ ላይ ለመኖር በሚደረገው ጥረት፡ የሰው ልጅ መንቀሳቀስን በሚመለከት በሰብኣውነት እየታሰበ ለስደት ትልቅ ቦታ መስጠት ግድ ነው።

ይህንን “ስደተኞችን ለምትደግፍና ከስደተኞች ጋር ለምትተባበር ኤሮፓ እንስራ!” (Pour une Europe migrante et solidaire)የሚባለው ማኒፈስቲ የምንፈርመው፡ ኤሮፓ ሁሉንም የተፈናቀሉ በመሬቷ የምትቀበልና እንደ ኣፍሪቃና መካከለኛ ምስራቅ የመሳሰሉት የጦርነትና የድህነት አካባቢዎች ህዝቦች ስቃይ የሚገባት እንድትሆን ስለምንመኝ ነው።

ይህንን “ስደተኞችን ለምትደግፍና ከስደተኞች ጋር ለምትተባበር ኤሮፓ እንስራ!” (Pour une Europe migrante et solidaire) የሚባለው ማኒፈስቶ የምንፈርመው፡ ኤሮፓ በስደትና በማሕበራዊ መወሃሃድ ረገድ፡ በኮምዩኒቲ ፕሮጀክቷና በአገርና ብውጭ ፖሊሲዎቿ የመተጋገዝ ቫልዩዎቿ ተመልሳ እንድታገኝ ስለምንመኝ ነው።

ይህንን “ስደተኞችን ለምትደግፍና ከስደተኞች ጋር ለምትተባበር ኤሮፓ እንስራ!” (Pour une Europe migrante et solidaire) የሚባለው ማኒፈስቶ የምንፈርመው፡ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች በሚወሰዱበት የኤሮፓ ቦታዎች ለልዩ የህዝብ ተወካይነት ዕድል እንዲሰጥ ስለምንመኝ ነው።

ይህንን “ስደተኞችን ለምትደግፍና ከስደተኞች ጋር ለምትተባበር ኤሮፓ እንስራ!” (Pour une Europe migrante et solidaire) የሚባለው ማኒፈስቶ የምንፈርመው፡ ሁሉም ማሕበራዊ ትዋንያን የዕድመና ሌላ ልዩነት ሳይደረግ በእኩልነት የሚያበረክቱበት፡ መተጋገዝ እንጂ ሌላ ዓላማ የሌለው የስራ ሁኔታ እንዲፈጠር ስለምንፈልግ ነው።

ስደተኞችን መቀበል፡ ኤሮፓን ማቀፍ ማለት ነው።

 

Back To Top